የጁቤ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ግሬደር ፣ ኤክስካቫተር ፣ ሮለር ፣ ሻወር ትራክ ፣ ዶዘር በሰዓት ኪራይ ነዳጅ እና መጓጓዣ ተጫራቹ ችሎ ፣ ገልባጭ መኪና ጠጠር በሜትር ኩብ ነዳጅ ተጫራቾች ችሎ በማጓጓዝ የጠጠር መንገድና ጠረጋ ስራ ፣ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ ፣ ፕሪንተር እና ላፕቶፕ ከነሙሉ አክሰሰሪው በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
- ሎት1.ግሬደር ፣ ኤክስካቫተር ፣ ሮለር ፣ ሻወር ትራክ ፣ ዶዘር በሰዓት ኪራይ ነዳጅ እና መጓጓዣ ተጫራቹ ችሎ ፣ ገልባጭ መኪና ጠጠር በሜትር ኩብ ነዳጅ ተጫራቾች ችሎ በማጓጓዝ የጠጠር መንገድና ጠረጋ ስራ ፣
- ሎት2. የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት3. ፕሪንተር እና ላፕቶፕ ከነሙሉ አክሰሰሪው በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው የሚሳተፍ
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው።
- የተሞላው ዋጋ ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር /በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) የተመዘገቡ እና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያያዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠ/ዋጋ ላይ 1% አንድ ፐርሰንት /በcpo በጥሬ ገንዘብ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ የሚችሉ።
- 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የማሽን ኪራይ 200/ሁለት መቶ ብር/ ፣ የጽህፈት መሳሪያ ፕሪንተር እና ላፕቶፕ ከነሙሉ አክሰሰሪው 100/አንድ መቶ ብር/ከፍለው ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ከቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል በአንድ ፖስታ ኮፒ ፣ በአንድ ፖስታ ፣ cpo በአንድ ፖስታ በማሸግ 3ቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት። በተገለፀው የጊዜ ገደብ ውል ያልፈፀመ እንደሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን ገንዘብ መ/ቤቱ ውርስ ያደርጋል።
- ውድድሩ በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ የሚለይ በመሆኑ ተጫራቾች ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ መሙያው ሰነድ ላይ ምን ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውጭ ይደረጋል። ስለሆነም በጥንቃቄ መሞላት አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን በአየር ላይ ውሎ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሠዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 በግልጽ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱና በፖስታዎች ላይ ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 246 0070/0004 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ጎጃም መስተዳድር ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ
የጁቤ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
