የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ ባለብት ዶ/ር ፉፋ ደዎ የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ አለሜ ሀብቴ መካከል ስላለው ፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/184915 በ18/4/2014 ዓ.ም. እና በኮ/መ/ቁ/105402 በ16/3/2015 በ17/05/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ቀለበት መንገድ ሳይት የቤት ቁጥር BRR-B4-3(06) የሆነው ባለሁለት መኝታ ኮንደሚኒዬም ቤት የቦታው ስፋት በፕሮፖርሽን 41.2908 ካ.ሜ. የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር (412,980) የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል ሆኑ ታውቆ ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለስብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ ሆኑን እንገልፃለን።
በፈዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
