በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት የስቴሽነሪ ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ እንዲሁም አላቂ የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2015
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት በወረዳው ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሶስተኛው ዙር ጥቅል የእቃ ግዥ ማለትም:_
1. 1. የስቴሽነሪ ዕቃዎች 2. የደንብ ልብስ 3. አላቂ የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል። በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
2. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘኑን ግብር የከፈሉ፣ ከገቢዎች hሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 -6:30 ከሰዓት 7:30-11፡30 በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ትችላላችሁ።
5. ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ አለባቸው፤ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማሰራት ይኖርበታል። የባንክ ቼክ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን። በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው። ለጥቃቅንና አነስተኛ የጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ ትብብር የሚል አንቀበልም፤ የጨረታ ዋስትና ደብዳቤ ተብሎ መጻፍ አለበት።
|
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር |
የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ብር |
|
ሎት 1 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
100 |
3000 |
|
ሎት 2 |
የደንብ ልብስ |
100 |
3000 |
|
ሎት 3 |
አላቂ የጽዳት እቃዎች |
100 |
3000 |
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን መሥሪያ ቤቱ በሰጣቸው የአንዱ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስና ጠቅላላ ዋጋ በሚሰጠው ቦታ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም ፊርማና ሙሉ ስም አድራሻቸውን በመግለጽ ከአንድ ኦርጅናል ኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ዓይነት ለለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።ናሙና ካላቀረቡ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም።
8. የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል በዚሁ ቀን 4፡30 ጨረታ ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። በመሆኑም ከተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ውጪ የሚቀርቡ ማንኛውም የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
9. የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. ለጨረታው የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው። ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ወጪ በማዘዝ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ፋ/ጽ/ቤት ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
1. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተገኙባቸው ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ከጽ/ቤት ጋር የግዥ ውል ስምምነት በመፈራረም ከተፈረመበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 7(ሰባት) የሥራ ቀናት ዕቃዎችን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ እና 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ማንኛውም ተጫራች ዋጋውን በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
14. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ከመገናኛ ወደ 24 ኮከብ ህንጻ አጠገብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 860 0233 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
