ቡና ባንክ አ.ማ. የዕቃዎችና የአገልግሎት አቅርቦት ለአንድ ዓመት መዝግቦ በመያዝ በውስን ጨረታ ለሚፈፀሙ ጥቅል ግዥዎች በፕሮፎርማ ግዥና እንዲሁም በቀጥታ ግዥ ሂደቶች በማሳተፍ ግዥዎችን መፈፀም ይፈልጋል
የአቅራቢዎች ዝርዝር ምዝገባ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር BB/006/2023
ቡና ባንክ አ.ማ. ቀጥሎ ባለው ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱትን የዕቃዎችና የአገልግሎት አቅርቦት ዘርፎች መስፈርቱን ማሟላት የሚችሉና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢ ድርጅቶች ቀጥሎ ከ1-8 ተ.ራ ቁጥር በተዘረዘሩ ነጥቦች ላይ በመመስረት ብቁ አቅራቢዎችን(Potential Suppliers)(መምረጥ በሚመለከታቸው የአቅርቦት ዘርፍ በአቅራቢነት ዝርዝር(Supplier List) ለአንድ ዓመት መዝግቦ በመያዝ በውስን ጨረታ ለሚፈፀሙ ጥቅል ግዥዎች ፤ በፕሮፎርማ ግዥና እንዲሁም በቀጥታ ግዥ ሂደቶች በማሳተፍ ግዥዎችን መፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም ቀጥሎ የተጠቀሱትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማቅረብ የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ10 ተከታታይ ሥራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተመዝጋቢ ድርጅቶች ከተመዘገቡበት ዘርፍ ጋር ተዛማጅ የሆነ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የመንግስት የግብር ግዴታ መወጣትን የሚያመላክት ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ)የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ሚያዝያ 7 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ይችላል።
- ድርጅቶቹ ከተመሰረቱ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ከሆነ በውጭ ኦዲተሮች የተሰራ የቅርብ ሁለት ዓመታት ወይም የአንድ ዓመት የፋይናንሺያል ኦዲት ሪፖርት ማቅረብ አለባቸው።
- ተመዝጋቢ ድርጅቶች ቀደም ባሉት ጊዜያት በገቡት ውል መሰረት ግዴታቸውን(በመጠን ፣ በጊዜና በጥራት)የተወጡ መሆኑን የሚገልፅ ቢያንስ የሶስት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው።
- ተመዝጋቢ ድርጅቶች የአምራች ድርጅቶች ከሆኑ የጥራት ስራ አመራር ሥርዓት(QMS of ISO 9001:2015) የተገበሩና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተመዝጋቢ ድርጅቶች የአምራች ድርጅቶች ህጋዊ ወኪል ከሆኑ ውክልና የተሰጠው አስመጪ እና ጅምላ አከፋፋይ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ (Manufacturer's Authorization Letter) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተመዝጋቢ ድርጅቶች ባንኩ የሚፈልጋቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በተፈለገው ጥራት ፣ መጠን ፣ ጊዜ ቦታና ሁኔታ ለማቅረብ ፈቃደኛ እና ኃላፊነት የሚወስዱ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተመዝጋቢ ድርጅቶች ተወዳድረው ላሸነፉበት ዕቃዎች ከባንካችን ጋር የረጅም ዓመታት ውል (Framework Contract Agreement) በመግባት የአቅርቦት ስራ ለማከናወን ፈቃደኞች መሆናቸውን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
- ተመዝጋቢ ድርጅቶች ተወዳድረው ላሸነፉበት ዕቃዎች በተጠየቀው ቦታ ድረስ ዕቃዎቹን ለማቅረብ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማቅረብ ፈቃደኛ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
በመሆኑም ተመዝጋቢዎች ምንም ዓይነት ክፍያ መክፈል ሳይጠበቅባቸው ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ቦሌ መንገድ ሩዋንዳ ኤንባሲ መታጠፊያ ላይ በሚገኘው በባንኩ ዋና መ/ቤት የግዥ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ስራ ቀናት መመዝገብ የሚቻል መሆኑን እየገለፅን ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የሚመጣ የማንኛውም አቅራቢዎች ማስረጃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን።
|
S/N |
Description |
|
1 |
Maintenance Service (Vehicles, Generators, Note Counting Machine, Air Conditioner, Lift, Data Center, and Other Office equipment). |
|
2 |
Training and Employee Examination service |
|
3 |
Networking Service |
|
4 |
Security and Janitorial Service |
|
5 |
Interior Designing Service |
|
6 |
Construction Service |
|
7 |
Meter Taxi and Car Rental Service |
|
8 |
Hotels (4 Star and above) |
|
9 |
Vehicle Crane Service |
|
10 |
Languages Translators |
|
11 |
Vehicle Tow Service |
|
12 |
Event Organizing Service |
|
S/N |
Description |
|
1 |
Computers, Printers, and other IT Related Equipment |
|
2 |
IT Networking Items |
|
3 |
Note Counting Machines |
|
4 |
Generators |
|
5 |
Air conditioners |
|
6 |
Electronics Equipment |
|
7 |
Vehicles and Motor Cycles |
|
8 |
Spare parts, Tires, Battery Lubricants |
|
9 |
Stationery Items |
|
10 |
Printing Items |
|
11 |
Toners |
|
12 |
Building and Electrical Materials |
|
13 |
Cleaning Materials |
|
14 |
Agenda and Table Calendar |
|
15 |
Promotional Items and Give Away materials |
|
16 |
Office Furniture |
|
17 |
Other Office Equipment (Fire Extinguisher and others) |
|
18 |
Car Decor Items |
|
19 |
Shutter, Mesh Sticker, and Carpet |
|
20 |
Safe Deposit Boxes |
|
21 |
Wooden Counter and Aluminum Partition Works |
|
22 |
Light Box |
|
23 |
ATM Machine |
Tel: 011 158 0869/011 126 2144
"Bank of the Visionaries"
Bunna Bank
