የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የሰላም ማስከበር ማእከል G+3 (20-03B) ፕሮጀክት በስሩ ለሚያስተዳድራቸው የዋና መ/ቤት ግቢ ማስዋብ ስራ ፕሮጀክትና የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮጀክት የሚያስፈልጉ Cement Tiles as per sample and Cement Tiles 400x400x5 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SC/024/2015
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የሰላም ማስከበር ማእከል G+3 (20-03B) ፕሮጀክት በስሩ ለሚያስተዳድራቸው የዋና መ/ቤት ግቢ ማስዋብ ስራ ፕሮጀክትና የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮጀክት የሚያስፈልጉ፡
- Cement Tiles as per sample
- Cement Tiles 400x400x5 ብዛታቸው በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም:-
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት (17-06B) በስታፍ ኮሌጁ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የፕሮጀክት ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሽገ ኤንቨሎፕ እስከ ሚያዝያ 03 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 የጨረታ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ሚያዝያ 03 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ - የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተፕራይዝ
የጃንሜዳ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት (17-06B)
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 895 9810 / 011 812 1352
6 ኪሎ( ወደ ፈረንሳይ ቤላ መንገደ መሄጃ) የሚገኘው የመከላከያ አዣዝነትና ስታፍ ኮሌጀ ካንፕ ውስጥ
