አቢሲንያ ባንክ በዋስትና የያዘውን ንብረት ለመሸጥ ይፈልጋል
መጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል: በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (ኢማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ: ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ በከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል:
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስርያ ቤት የነበረው ህንፃ ጎን ካለው አልፓውሎ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በባንኩ የሕግ መምሪያ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 0711 እና 011 554 0341 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
የተበዳሪው ስም |
ከተበዳሪ ሚፈለግበት |
የመያዣ |
የንብረቱ አይነት |
የቦታ ስፋት |
ባለቤትነት ማረጋገጫ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰአት |
የጨረታ ሰአት |
|
አቶ ሰለሞን ሀይሉ ገዩሀንስ |
እስከ ነሐሴ 25 ቀን |
ተበዳሪው |
ግንባታጩ 80% |
175.00 ካሜ |
ቦሌ7/62/8/9/251874/ |
አዲአበባ ከተማ |
25,606,108.14 |
ግንቦት 02 ቀን |
4:30-5;30 |
5፡30-6፤00 |
