በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Conveyor Belt በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/Re-36/2015
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Conveyor Belt በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 115.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዢ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች በጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም C.P.O ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዢ መምሪያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው በእለቱ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዢ መምሪያ ይከፈታል። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 442 0216 ፋክስ 011 442 0688
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
