የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት መኖሪያ ቤት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት የተረከባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሽያጭ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው/መያዣ ሰጪው ስም |
የንብረቱ ዓይነት |
የንብረቱ አድራሻ |
የቦታው ስፋት በካ/ሜትር |
የጨረታ መነሻ ሽያጩ ዋጋ/ብር |
የሽያጭ ሁኔታ |
|
1 |
መለያ ኢብራሂም/ ኢስማኤል ሀሩን |
መኖሪያ ቤት
|
ምዕራብ ሐረርጌ ግራዋ ከተማ ቀበሌ 01 |
375 ካ/ሜ
|
259,195.24
|
የመጀመሪያ የጨረታ ሽያጭ
|
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው ሚያዚያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 5፡30 በገለምሶ የባንኩ ቅርንጫፍ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ይካሄዳል።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ደብዳቤው ከደረሰው ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት። ባይከፍል ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ፣ የሊዝ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን የስም ማዛወሪያ ጨምሮ ገዢው አሸናፊው ይከፍላል።
- አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸነፉት የጨረታ ተሳታፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ለጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ከባንኩ ገለምሶ ቅርንጫፍ ጋር ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት
