የሰቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የውሃ የመስመር ማከፋፈያ ግንባታ ፣ የተለያዩ ግንባታዎች እና የህንፃ መሳሪያዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ብሄራዊ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የሰቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለወረዳው በ2015 ዓ.ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተገለጸውን ግንባታ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- 01 ቀበሌ ጋቖ ትም/ቤት የውሃ የመስመር ማከፋፈያ ግንባታ
- የተለያዩ ግንባታዎች
- የህንፃ መሳሪያዎች
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የ2015 ዓ.ም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥ መጠናቸው ከብር 20000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የእቃው እና የግንባታው አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 ለተገለጸው ግንባታ እቃ ግዥ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከግዥ/ን/አስ/ር/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ።
- ለግንባታ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ21/ ለሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ለእቃ ግዥ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሰቆጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመ/ሂ-1 ገቢ አድርጎ ኮፒውን ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእቃ ግዥ ከ22/7/2015 እስከ 6/8/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው። በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸው ፊርማቸውን ሙሉ አድራሻ የድርጅቱ ማህተም መሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ7/8/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ግዥ /ን/አስ/ር ቡድን 5 ይከፈታል። ለግንባታ ግዥ ከ22/7/2015 እስከ 12/8/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው። በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸው ፤ ፊርማቸውን ፤ ሙሉ አድራሻ የድርጅቱ ማህተም ማሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ13/8/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ግዥ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ የዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /መሂ- በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ጀምሮ በ5 ተከታታይ ስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አስይዘው ውል ካልፈረሙ መ/ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው።
- መ/ቤቱ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 ለቀረቡት የጨረታ ሰነድ ማንኛውም ህጋዊ ተወዳዳሪ የሚወዳደርባቸውን የጨረታ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡት የግንባታ ዝርዝሮች በቀረበው የስራ ዝርዝር መሰረት ሙሉ በሙሉ የመሙላት ግዴታ አለበት።
- አሸናፊው የአሸናፊውን ንብረት ከሚፈለግበት መ/ቤት ንብረት ክፍል አቅርቦ በስሙ ገቢ የማድረግና ሂሳቡን በስሙ የማወራረድ ግደታ አለበት።
- በጨረታው ቅሬታ ያላቸው ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተና አሸናፊው ከተለየ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ባለው ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካል ማቅረብ አለባቸው። ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ አቤቱ ተቀባይነት የለውም።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 0416 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የሰቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
