የለኩ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ5(አምስቱም) ቀበሌያት የተመረተ የጠጠር መንገድ ግንባታ ስራ ቦርቻ ጠጠር/ selected material/ ሴሌክት ማቴሪያል ደቃቅ ጠጠር በሲኖትራክ መኪና ባለ16 m3 ሜትር ኩብ የሚይዝ ለአምስቱም ቀበሌያት በተመረጡ ቦታዎች ለመጣል /DUMP/ ለማድረግ GC-5 & BC-5 እና ከዚህ በላይ የሆኑትን ተጫራቾችን ነዳጅን ጨምሮ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የለኩ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በለኩ ከተማ አስ/ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ለ5(አምስቱም) ቀበሌያት የተመረተ የጠጠር መንገድ ግንባታ ስራ ቦርቻ ጠጠር/ selected material/ ሴሌክት ማቴሪያል 500 /አምስት/ ቢያጆ ደቃቅ ጠጠር በሲኖትራክ መኪና ባለ16 m3 ሜትር ኩብ የሚይዝ ለአምስቱም ቀበሌያት በተመረጡ ቦታዎች ለመጣል /DUMP/ ለማድረግ GC-5 & BC-5 እና ከዚህ በላይ የሆኑትን ተጫራቾችን ነዳጅን ጨምሮ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁም መሰረት ፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- ተመዝጋቢ የሆኑ
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የመልካም ስራ አፈፃፀም ያላቸው
- የ2015 ዓ.ም የንግድ ስራ ፈቃዳቸው ያሳደሱ
- የጨረታ ዶክሜንት ሰነድ 1(አንድ) ኦርጂናል እና ሁለት (2) ኮፒ ማቅረብ የሚችል የቦርቻ ጠጠር ትልልቅ ድንጋዮችን ቀላቅሎ ያመጣ የብያጆ ክፍያ አፈጻጸም መ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እና የራሱ ኪሳራ ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት።
የቦርቻ ጠጠር ድንጋይ ሴሌክት ማቴሪያል በአግባቡ በየ3 ሜትር ርቀት መጣል አለበት። የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር 20,000 (ሃያ ሸህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ የሚችሉ የማይመለስ 200(ሁለት መቶ ብር) በገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል የስራ ዝርዝር ሰነድ የሚያሳይ ከለኩ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ለ15(አስራ አምስት ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የቦርቻ ጠጠር ድንጋይ ደቃቁን የአንድ ሜትር ኩብ/m3/ ቢያጆ ዋጋና ጠቅላላውን የሚያመጡበትን በመግለጽ በፖስታ አሽጋችሁ ዘወትር በስራ ሰአት ለኩ ከተማ አስ/ፋይናንስ ጽ/ቤት በግ/ፋ/ስራ ሂደት ከፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማኖር ይችላሉ። ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባልተገኙበት/ በ16ኛው ቀን የፖስታው ሳጥን በእለቱ በ8፡30 ሰዓት እስከ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜ ፣ እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
ማሳሰቢያ መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በሲዳማ ክልል የለኩ ከተማ አስ/ፋይናንስ ጽ/ቤት
