Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Oct 2022, 12:34 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ ባለመብት አቶ ደሮዛ ዳዋና ዳጌሮ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ በላይነሽ መሀመድ ይመር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 177340 193448 በ5/8/2014 ዓ.ም. እና በ20/4/2014 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የቤ.ቁ ቢ40/17 የሆነ ቤት በአመልካች ስም ተዝግቦ የሚገኝ ቤቱ ዕዳ የባንከ ብር 379,158.34 ያለበት ሆኖ የተመዘገበ ግማሽ ኮንዶሚኒየም ቤት ካ/ቁ 9112/18144/50 የቤቱ ስፋት 106-46 ካ/ሜትር የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 425,840 (አራት መቶ ሃያ አምስት ሺ ስምንት መቶ አርባ ብር ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንበረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ cPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬhቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል  ፍ/ቤቶች

የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender