በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የህብረት ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ብርድ ልብስ ፣ ወታደራዊ ካልሲ ፣ አንሶላ እና ፕላስቲክ ምንጣፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የህብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ አቅርበው መሆን አለበት፡፡
|
ተ/ቁ |
የጨረታው ዓይነት |
የመዝጊያና የመክፈቻ ቀን |
|
ሎት-1 |
ብርድ ልብስ |
ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 |
|
ሎት-2 |
ወታደራዊ ካልሲ |
ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 |
|
ሎት-3 |
አንሶላ |
ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 8:30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 |
|
ሎት-4 |
ፕላስቲክ ምንጣፍ |
ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 8፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 |
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለተጨማሪ ዕሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ፣ የአቅራቢነት የድህረ-ገፅ ምዝገባ የምስክር ወቀረት ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የቲን ሰርተፍኬት ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት እና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት የግዥ አዋጅ መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
- ከላይ በመግለጫ ለተጠቀሱት የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዶችን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 8 በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ። የጨረታው ሰነድ የሚቀርበው በአካል ቢሮ ድረስ በመምጣት ሲሆን ከዚህ በላይ በዝርዝር ከተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ዉጭ ዘግይቶ ለሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በሀርድ ኮፒ በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ያልተካተቱ የተለያዩ የጨረታ መመሪያዎች ስላሉ ማንኛውም ተጫራች በሶፍት ኮፒ ለመውሰድ ባዶ ሲዲ ብቻ ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ከጨረታ መክፈቻ ቀን አስቀድሞ ባሉት ቀናት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም።
- መስሪያ ቤታችን እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የተሰማሩበትን ዘርፍ የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ሳያመጡ የጨረታ ሰነድ መግዛት አይቻልም።
- አድራሻ ህብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ (ጦር ሃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት)
ስልክ ቁጥር 011-3-71-19-48
ስልክ ቁጥር 011-3-72-73-14
ፋክስ ቁጥር 011-3-71-09-01
በሀገ መከላከያ ሚኒስቴር የህብረት ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ግዥ ቡድን
