Tender Detail

Tender Details

  • Deadline04 Oct 2022, 12:51 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የመኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ወ/ሮ አባይነሽ ዳጌሮ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ደልቦ ደንድሮ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 216833 በ29/11/ እና በመ/ቁ 137483 ጥር 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ውስጥ የሚገኝ ቤቱ ቁጥር 457 የሆነ መኖሪያ ቤት ፍርድ ያረፈበት በቁጥር ወ/12/ 021101/431/11502/00 የተመዘገበ የተነፃፃሪ ካርታ ያለው የቦታው ስፋት በተነፃፃሪ ቤቱ ያረፈበት 42.95 ካ.ሜ ጠቅላላ የቤ/ቁ በፕሮፖርሽን የሚደርሰው 73.34 ካ.ሜትር መሆኑ ታውቆ ጠቅላላ የጊቢ ስፋት 15.22 መንገድ የሚነካ ሆኖ ተጠቃቃሽ መዝገብ ያለበት ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 27,847,62 ሃያሰባት ሺ ስምንት መቶ አርባ ሰባት ብር ከ62 ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። የሐራጁ ሽያጭ  የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም።በጨረታው አሸና የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።

በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።

 በፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender