የጉምሩክ ኮሚሽን ጅጅጋ ቅጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ፣ የቤት ማስዋቢያ ፣ ህንፃ መሳሪያ ፣ አልባሳት ፣ የቤት ዕቃ ፣ ስፔርፓርትስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅጅጋ ቅጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ፣
- የቤት ማስዋቢያ ፣
- ህንፃ መሳሪያ ፣
- አልባሳት ፣
- የቤት ዕቃ ፣
- ስፔርፓርትስ ፣ ልዩልዩ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ከ17/2/2014 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል። በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የዘርፍ ንግድ ፍቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈለ እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ [CPO/ ለግልፅ _ ጨረታ የመጫረቻውን 5% (ፐርሰንት) ማስያዝ የሚችል፤
- ለግልፅ ጨረታ ቅ/ፅ/ቤቱ ካስቀጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ዕቃ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን የሚረከብ መሆን አለበት።
- ዕቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ያላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያው ይመለስላቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅጅጋ ቅርንጫፍ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ አሰርቶ ማምጣት አለበት።
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃዎቹን ካሸነፉ በኋላ ከጅጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
- ተጫራቹ ዕቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን ኣይወስድም።
- ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ነሃሴ 19/12/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 200 እስከ 3፡45 በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ ቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው 3፡45 ተዘግቶ በ19/12/2014 ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
N.B. አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% ፐርሰንት የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
