የመከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ የ PPR Pipe, Fittings and UPVC Materials ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SM/102/2022
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ ምስራቅ ዕዝ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት ከዚህ በታች የቀረቡትን የ PPR Pipe, Fittings and UPVC Materials ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የስራ ዝርዝር |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
1 |
PPR Pipe, Fittings and UPVC Materials |
DCE/SM/102/2022 |
27/12/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 |
27/12/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 |
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታhስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመከፈል ዘወትር በስራ ስዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር መመርያ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ሞዴል ብቻ ነው። በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34/33
ማዞሪያ 011442-22-70/71/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሪላ ግቢ
www.dce-et.com
Email:- Info@dce-et.com
መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
