Tender Detail

Tender Details

  • Deadline02 Oct 2022, 10:20 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Promotional Items

በደቡቡ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ ሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2015 በጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡቡ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ ሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2015 በጀት ዓመት የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት -

  • ሎት 1. አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣
  • ሎት 2. የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣
  • ሎት 3. የጽሕፈት መሣሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 4. የባለሙያ ደንብ ልብስ ጨርቅ ፣ ስፌት አገልግሎት እና የህሙማን አልባሳት
  • ሎት 5. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • ሎት 6. የውሃና ኤሌክትሪክ ዕቃዎች ሲሆኑ፡

ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን።

  1. በዘርፉ የተሰማራ የንግድ ፍቃድ ያለውያላት
  2. የ2014/2015 ዓም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችልየሚትችል
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የሚትችል
  4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነች
  5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No/ ያለው|ያላት
  6. የ2014 ዓ/ም ግብር ከፍሎ ያጠናቀቀች
  7. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የሚትችል
  8. የ2014 በጀት ዓመት መልካም የአፈፃፀም ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የሚትችል
  9. ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማቅረብ አለባቸው።
  10. እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በብር 100 (አንድ መቶ) ብር ብቻ ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 15 ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር - 7 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  11. ጨረታው የሚከፈተው በ16 ኛው ቀን በ3:00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ባይገኙ ጨረታውን መክፈት ያዳግትም።
  12. የጨረታ አሸናፊው የባለሙያ ደንብ ልብስ ጨርቅ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል። በናሙናው መ/ቤቱ ካልተስማማ መ/ቤቱ ራሱ በሚያቀርበዉ ናሙና መሠረት ይሆናል።
  13. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ተቋሙ ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርበታል።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:
  15. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር- 046 777 0602 በደወል ማግኘት ይችላሉ። 

ማሳሰቢያ - የጨረታ መዝጊያና መከፈቻ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ህዝባዊ በዓል ባለበት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል

በደቡብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ በጎፋ ዞን ጤና መምሪያ ሳውላ ጠቃላይ ሆስፒታል

Save Tender