Tender Detail

Tender Details

  • Deadline08 Sep 2022, 12:14 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. ወላይታ ሶዶ ዲስትሪከት ጽ/ቤት 2014 ዓ.ም. በጀት ለሚያስገነባው የማስፋፊያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ኦሞ ማይከሮ ፋይናንስ(አ.ማ) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪከት ጽ/ቤት 2014 ዓ.ም በጀት ለሚያስገነባው የማስፋፊያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች(ሎት-1 ድጉና ፋንጎ ፣ ዳሞት ጋሌ ፣ ዳሞት ወይዴ ፣ ዳሞት ፑላሳ ፣ ሁምቦ ወረዳዎች) ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚችሱ የሥራ ተቋራጮች፡

  1. ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡ ደረጃቸው GC-4/BC-4 እና ከዛ በላይ የሆኑ፤ ግብር በመክፈል በ204 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ምስከር ወረቀት ያላቸው ተkታ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ ቲን(TIN) መለያ ቁጥር ያላቸው ፣ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ምስhር ወረቀት ያላቸው ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ወቅታዊ ታስ ሊራንስVALID TAX CLEARANCE/ ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚች።
  3. ተጫራቾች በፈዴራል ግዥ እና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 700.00(ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ (ኢማ) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር----የንግድ ፈቃዳቸውን ዋናውን/Original/ በመያዝ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ/ ባንክ ጋራንቲ 500,000.00(አምስት መቶ ሺ ብር) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የግንባታ ሳይቶችን ጉብኝት ተደርጎ ከወረዳው ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ቢሮ የሳይት ጉብኝት ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሠነድ ኦሪጅናሉን እና ቴከኒካል ሠነድ ኦሪጅናሉን አንድ ላይ በማሸግ እና 2 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸ ኤንቨሎፕ ሁሉንም ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውንና የፕሮጀክቱን ስም በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ30 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8:30 ሰዓት በኦሞ ማይከሮ ፋይናንስ(ኢማ) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ግ/ፋን/ስ/ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር3G+2 ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
  10. ተጫራቾች በጨረታ መፈቻ ዋጋና በሂሳብ ማስተካከያ ዋጋ ልዩነት ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ መሆን የለበትም።
  11. ተጫራቾች በዞኑ ውስጥ ሲሰሩ ምንም ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው መሆን አለባቸዉ።
  12. በተጨማሪ እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የደ/ብ/ብ/ሕ//መንግት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 ፣በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የወጣ የኮንስትራከሽን ብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 648/2013 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማሻሻያ የያዘ ሰርኩላር ተግባራዊ ይሆናል።
  13. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ በስቁ. 046 552 4450 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ(አማ) ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት

 

Save Tender