Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Aug 2022, 12:11 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Promotional Items

የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ህትመቶች ፣ ለደንብ ልብስ ተጠቃሚ ሠራተኞች የሚሆን ሸሚዝ እና የህፃናት መታቀፊያ ፎጣዎች ፣


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህሙማን ህክምና አገልግሎት የሚዉሉ

  • የተለያዩ ህትመቶች ፣
  • ለደንብ ልብስ ተጠቃሚ ሠራተኞች የሚሆን ሸሚዝ እና የህፃናት መታቀፊያ ፎጣዎች ፣
  • የፅህፈት መሳሪያዎች እና
  • ኤሌክትሮኒክስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራትና ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በዚህ ጨረታ የሚወዳደሩ ድርጅቶች፡-

  1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በግንባታ ዘርፍ ለሚሳተፉ የታደሰ የሙያ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  2.  የግብር ከፋይነት መለያ (ቲን) ያላቸው።
  3. አጠቃላይ የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. አጠቃላይ ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።
  6. ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት (ማግኘት) ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማንኛውንም ግብር ጨምሮ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡15 ይታሸጋል።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ4፡30 ይከፈታል። ቀኑ በዓል (ዝግ )ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ (ማብራሪያ) ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 57 38/058 222 09 16 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender