የኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ስልጠና ለሰራተኞች ለመስጠት የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር OEU/PLW & F/NCB-04/2015
የኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ስልጠና ለሰራተኞች ለመስጠት የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የስራው ዓይነት |
የሰልጣኝ ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን |
|
1 |
የባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ስልጠና አገልግሎት ግዥ |
120 |
7,000.00 |
ጨረታው ነሀሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል። |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በድርጅታችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር (1000475084245 EEU OROMIA REGION) የማይመለሰ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ዘውትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ፕሮኪዩርመንት ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንh በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 011 522 6131 መደወል ይችላሉ።
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኦሮሚያ ክልል
ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
