የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ አይነት ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታቂያ
ቁጥር WSSF/LP/005/2022
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ አይነት ግዥዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
|
ምድብ |
መግለጫ (Descriptions) |
|
1 |
የሠራተኛ ማመላለሻ መኪና ኪራይ (ባለ 60 ወንበር), የፍሳሽ ቆሻሻ ማንሻ መኪና ኪራይ |
|
2 |
የሠራተኛ ማመላለሻ መኪና ግዥ (ባለ 29-30 ወንበር)፣ የትራከተር ግዥ |
|
3 |
ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካሎች (ግብአቶች)፣ የውሀ ማጣሪያ ግብአቶች |
|
4 |
የተለያዩ ጎማዎች, የውስጥ ላስቲኮች, መለጠፊያዎች( Vehicles and machinery tyres, inner tubes and Tube Patches) |
|
5 |
የአረም, የተባይ, እና የፈንገስ መድሀኒቶች (herbicides, insecticides and fungicides) |
|
6 |
የተለያዩ የመከላከያ አልባሳት፣ ሳሙና፣ ቫዝሊን፣ የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎችም |
|
7 |
ስቴሽነሪ (Photo copy paper and different printing materials) |
|
8 |
የወርክሾፕ ሥራዎች የጥገና ግዥ |
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) ለየምድቡ ለየብቻ በመhፈል ከላይ ለተጠቀሱት ግዥዎች በየምድቡ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በመግዛት በጨረታው መወዳዳር ይችላሉ። ወንጂ/ሽዋ ስኳር ፋብሪካ ሜክሲኮ ፌሲፕስ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢ ቁT 301 አዲስ አበባ ተጨማሪ መረጃ 011 551 6082/011 558 5229/
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባን በተረጋገጠ ዋስትና በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴከኒካል በየምድቡ ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ከመሆኑ በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ ሰባት ሰአት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 305 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚሆን ሲሆን ትክክለኛው የሥራ ቀን/የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነድ ውስጥ የሚጠቀስ ይሆናል።
- ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ
