Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Aug 2022, 10:33 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Promotional Items

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት (ለማሰራት) ይፈልጋል


የ2015 ዓ.ም. 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ

ማስታወቂያ ቁጥር 001/2015 ዓ.ም.

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት (ለማሰራት) ይፈልጋል።

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ''

  1. የአገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የአገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የአገር ውስጥ ተጫራቾች የ2014 በጀት ዓመት የታደሰ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
  4. የአገር ውስጥ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችለ መሆን አለባቸው።
  5. ሎት 1፤ሎት 2 ፤ ሎት 3 ፤ ሎት 5 ፤ ሎት 6 እና ሎት 9 ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ባሉት 10 ቀናት ውስጥ የዕቃውን ናሙና በዝርዝር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል በተጨማሪም ናሙና ያልቀረበበት የእቃ ይነት ከውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እንገልጻለን። እንዲሁም ሎት 4 ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ግን ወድድሩ በዋጋ ከተለየ በኋላ ቦታው ድረስ በመሄድ ጥራቱ የሚረጋገጥ እና አሸናፊውን ድርጅት የሚለይ ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ በእያንዳንዱ ሎት ማለትም ከሎት 1 እስከ ሎት 11 ያሉትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 5,000.00 (አምስት ሺ ብር) በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ./C.PO/ ብቻ ማቅረብ አለባቸው። በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል መደራጀታቸውንና በጨረታ ስራ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ሆን አለባቸው።ስ
  7. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡3o ሰዓት ለእያንዳንዱ ማለትም ከሎት 1 እስከ ሎት 11ያሉትን ለሚገዙ ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የድሮ ዘርፈሽዋል ት/ቤት አዲሱ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በመውሰድ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ኢንቨሎፕ ኮፒና ኦሪጅናል በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን (ተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. ጨረታው በ11ኛው 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የድሮ ዘርፈሽዋል ት/ቤት አዲሱ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 ይከፈታል።

የሎት ቁጥር

የዕቃው አይነት

ሎት 1

አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ኮድ 6212 እና 6219

ሎት 2

የፅዳት ዕቃዎች ኮድ 6218

ሎት 3

የሰራተኞች ደንብ ልብስ ኮድ 6211

ሎት 4

ኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ ዕቃዎች ኮድ 6314

ሎት 5

የተለያዩ የህትመት አይነቶች

ሎት 6

የመኪና ጎማ ኮድ 6241

ሎት 7

የተለያዩ የመስተንግዶ አይነቶች

ሎት 8

የሚኒባስ ታክሲ ኪራይና የመሳሰሉት

ሎት 9

የተለያዩ የመኪና ጌጣጌጦችና የመሳሰሉት

ሎት 10

ፈርኒቸር እና የመሳሰሉት ኮድ 6313 /የስቶር መደርደሪያ ሼልፍ ብቻ/

ሎት 11

ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚያገለግል ድንኳን ሞንታርቦ ወንበር እና ጠረጴዛ እንዲሁም ጄኔሬተር የመሳሰሉትን ኪራይ

10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የማስያዝና የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።

11. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል መደራጀታቸውና የጨረታ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል

13. መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ካቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዥ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።

14 ለጨረታው የተሰጠው ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በቦሌ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የድሮ ዘርፈሽዋል ት/ቤት አዲሱ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 833 2270 ወይም 011 868 0696 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

 

Save Tender