በምዕራብ ወለጋ ዞን የኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽሕፈት መሣሪያዎች ፣ የጽዳት መሣሪያዎች ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ፣ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ፣ ፈርኒቸሮች ፣ የሕንጻ ግንባታ መሣሪያዎች
የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2015 በጀት ዘመን
- የጽሕፈት መሣሪያዎች ፣
- የጽዳት መሣሪያዎች ፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ፣
- ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ፣
- ፈርኒቸሮች ፣
- የሕንጻ ግንባታ መሣሪያዎች ፣
- የመንግስት ሠራተኞች የደንብ ልብስ ፣
- ፍራሾች ፣
- ብርድ ልብሶች ፣
- አንሶላ እና ትራስ ፣
- ሞተር ሳይክል ፣
- ጀኔሬተር ፣
- ፎቶ ኮፒ ፣
- ሞንታርቦ ፣
- ዲጂታል ቪዲዮ ካሜራ ፣
- ፕሮጀክተር ፣
- የተለያዩ ሕትመቶችና ማህተም ፣
- የውኃ ግንባታ መሣሪያዎች ፣
- የመኪናና ሞተር ሳይክል ጎማ በግልጽ ጨረታ ማሰታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
መስፈርት:-
- ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2014 የንግድ ፍቃዳቸው ያሳደሱ ፣ ከሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገበበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክሰ (VAT) የተመዘገቡ መሆኑ ሕጋዊ ሰነድ ማቅረብ የሚችል።
- ያሸነፉበትን ዕቃ በተፈለገበት ጊዜ እስከ ኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንሰፖት አምጥቶ ለማስረከብ የሚችል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት። ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ካቀረቡ ተቀባይነት አይኖረዉም።
- በወረዳው የገንዘብ ጽ/ቤት የገበያ ጥናት ተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆኑ።
- ተወዳዳሪው ለጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተጠየቁትን ዕቃ ሁሉ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። አለበለዚያ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ።
- አሸናፊው ያሸነፈበትን ዕቃ ሁሉ በአንድ ላይ ውል በፈረመበት ጊዜ ውሰጥ ማቅረብ አለበት። በተናጠል ካቀረበ (አጠቃሎ ሳይጨርስ) ገንዘቡ አይሰጠውም።
የአቅራቢው ግዴታ፡
- የጨረታ ማሰታወቂያ ሠነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ለመግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሠነድ (የዕቃው ዝርዝር) ፋይናንስ ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ሁለቱንም በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ የራሱን ፊርማና የድርጅቱን ማህተም አድርጎበት በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚያቀርብ።
- የጨረታ ሠነድ(የዕቃው ዝርዝር) ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ሁለቱንም በአንድ ፖስታ በማሸግ የራሱን ፊርማና የድርጅቱን ማህተም አድርጎበት በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚያቀርብ።
- ሕጋዊ የካሸ ሬጅስተር ሰነድና በሀገር ውሰጥ ገቢዎች ባለሥልጣን ፍቃድ የታተመ ሰነድ መኖሩን ሕጋዊ ማሰረጃ ማቅረብ የሚችል።
- አሸናፈው የውል ስምምነት ማስከበሪያ በመመሪያ መሠረት አሸናፊ ከሆኑ ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውሰጥ ከጠቅላላው ግዥ 10% ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል።
- በተጠየቀው ዕቃ ሁሉ የሚሸጥበትን የአንዱ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ የሚችል ሙሉ በሙሉ ሞልቶ ያላቀረበ መወዳደር አይችልም ።
- ተጫራቾች (ተወዳዳሪው) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የዕቃውን ናሙና ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታው አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደ ተገለጸ እሰከ 15 ቀን ውሰጥ በኖሌ ካባ ገንዘብ ጽ/ቤት መጥተው ውል መፈረም አለባቸው። ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ የጨረታው ማሰከበሪያ ያሰያዘውን ገንዘብ ለመንግሰት ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዕቃ ከራሳቸው መጋዝን መኖሩን ከንግድና ገቢያ ልማት ጽ/ቤት ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
የጽ/ቤቱ መብት፡-
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው
ጨረታው የሚጠናቀቅበትና የሚከፈትበት ቀን፦
ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት ብቻ ይቆያል።
ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 የሥራ ቀናት በኖሌ ካባ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት የምትችሉና ተወዳደሪዎች (ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ቦታ በ22ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ሆኖም ቀኑ በዓል (የእረፍት) ቀን ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ሊጠይቁ ይችላሉ።
0917 35 44 11/057 632 0015/0979 57 92 90
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኖሌ ካባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
