የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል አቅርቦት ፣ የአልሙኒየም አቅርቦትና ገጠማ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች አቅርቦት፣ የመስታዎት አቅርቦትና ገጠማ ፣ የእንጨት በር አቅርቦትና ገጠማ ፣ ወተር ፕሩፍ ማቅረብና ማንጠፍ አርም ስትሮንግ ቦርድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማቅረብና ማሰራት ይፈልጋል
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ህንጻ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ
- ምድብ 1 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል አቅርቦት
- ምድብ 2 የአልሙኒየም አቅርቦትና ገጠማ
- ምድብ 3 የኤሌክትሪክ እቃዎች አቅርቦት
- ምድብ 4 የመስታዎት አቅርቦትና ገጠማ
- ምድብ 5 የእንጨት በር አቅርቦትና ገጠማ
- ምድብ 6 ወተር ፕሩፍ ማቅረብና ማንጠፍ
- ምድብ 7 አርምስትሮንግ ቦርድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማቅረብና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መከፈቻ ቀኑ በበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመከፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ በነፃ መውሰድ ይችላሉ
- ተጫራቾች የፋይናንሽያል ኦሪጅናል ሰነዶችን በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ የጠ/ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው እቃዎች በባለሙያ ተረጋግጦ ማለፍ አለበት፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል ፡፡
- የሚቀርቡና የሚገጠሙ እቃዎች በየፕሮጀክቱ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ገጥሞ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸውን እቃዎች ኢንተርፕራይዝ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉት 7 /ሰባት/የስራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለባቸው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 0930958351 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
