Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 Aug 2022, 10:04 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Generators

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ ተሽከርካሪዎች እና የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በልውና ዘመቻው ለተቋም አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን እና የጀነሬተር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ


በአብመ ገንዘብ ቢሮ የስ/ጎን/ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን

  • ሎት.1 ለህልውና ዘመቻው ለሚሰማሩ ተሽከርካሪዎች እና በዞኑ ስር ለሚገኙት መምሪያዎች መደበኛ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን
  • ሎት.2 በህልውና ዘመቻው ለተቋም አገልግሎት የሚውል የጀነሬተር ግዥ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ
    መግዛት ይፈልጋል::

ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባው፡-

  1. የግብር ከፋይ የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ብር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3.  ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም በመ/ቤቱ ዋና ገ/ያዥ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ እና ሲፒኦ ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ለግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና ከ1 በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  4.  ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50(ሃምሳ ብር) በመክፈል ሰ/ጎ/ዞን/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ጎንደር ዞን አሰተዳደር ደባርቅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 2/12 /2014 እስከ 16/12 /2014 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  8.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በቀን 17/12/2014 ዓ.ም. በ4፡00 ታሽጎ በ4:30 የከፈታል፡፡
  9.  አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን ከላይ በሎት ከ1-2 በተገለፁት መሰረት የተዘረዘሩትን ግዥዎች ለሰ/ጎን/ዞን ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ንብረት ክፍል ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡ የጨረታ ውድድር የሚካሄው በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፡፡
  11. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ ይህንን ጨረታ ከላይ በሎት ከ1-2 በተገለፁት መሰረት የተዘረዘሩትን ግዥዎች የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 0584170030/4006/ መጠየቅ ይችላሉ፡፡


የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ

Save Tender