Tender Detail

Tender Details

  • Deadline12 Aug 2022, 11:13 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Event Organizing And Planning

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 አስተዳዳር ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 አስተዳዳር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለወረዳው ጽ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1፡- አላቂ ዕቃዎችን፣
  • ሎት2፡- የደንብ ልብስ፣
  • ሎት3፡_ የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት4፡- የተሸከርካሪ ጎማዎች፣
  • ሎት5፡- የተሽከርካሪ እድሳት ጥገና፣
  • ሎት6፡- መስተንግዶ አገልግሎት፣
  • ሎት7፡- የትራንስፖርት አገልግሎት፣
  • ሎት8፡- የቢሮ ላተራልና ፈርኒቸር ጥገና፣
  • ሎት9፡- ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣
  • ሎት10፡- የህትመት አገልግሎት፣
  • ሎት11፡- የዲኮር ሞንታርቦ እና የድንኳን ኪራይ፣
  • ሎት12፡- ቋሚ እቃዎች

ስለሆነም በጨረታው መሳተ ሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶቾን አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል።

  1. ከዘርፉጋር ተያያዥ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ።
  2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ከ100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በላይ ከተጫረቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅብ አለባቸው።
  6. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ ጨረታው ያሸነፈበት መጠን ልክ 10% ማስያዝ አለበት።
  7. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 150.00 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ መውሰድ ይቻላል።ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 0.5% ማለትም ሎት1፡1500 ፤ ሎት2፡ 2000 ሎት3፡1500 ፤ ሎት4፡ 1000 ፤ ሎት5፡ 2500 ፤ ሎት 6፡ 1500 ፤ ሎት7፡1500 ፤ሎት8፡1000 ፤ ሎት 9 ፡1000፤ሎት 10 1500 እና ሎት 11 ፡1500 ፤ ሎት 12: 2500 በሚል pay/order ADDIS KTEMA K/K WERDA 10 F/TS/BET በሚል ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ለሁሉም ዕቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ሳምፕል ያልቀረበበትን ዕቃ የማናወዳድር መሆኑን እየገለጽን ሳምፕሉ ጨረታው ከመከፈቱ 3ቀን በፊት መቅረብ ይኖርበታል ከተጠቀሰው ቀን ዘግይተው የሚጡ ሳምፕሎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  9. የሚገቡት ዋጋዎች ቫት/ቲኦቲ ያካተቱ መሆን አለባቸው።
  10. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበት ዋጋና ከላይ የተጠቀሱትን ደጋፊ ሰነዶች 1 ኦሪጅናልና 1 ኮፒ በአንድ ላይ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቶች ጨረታውን ካሸነፉ በኃላ ያሸነፉበትን ዕቃ በወረዳው ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት፡- ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
  13. መ/ቤቱ የተሸለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኃላ ያሸነፉበትን የጨረታ አይነት ውል አልገባም ቢሉ ያሲያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ የሚደረግ እና ለ6 ወር የትኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት እንዳይሳተፉ የሚደረግ መሆኑን እንገልፃለን።
  • አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አጠና ተራ ከድልድዩ ከፍ ብሎ
  • ለበለጠ መረጃ በ011-273-8747(011-273-8842) በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 አስተዳዳር ፋይናንስ ፅ/ቤት

Save Tender