በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገ/ኢ/ልማት/ጽ/ቤት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገ/ኢ/ልማት/ጽ/ቤት ለወረዳ ለተለያዩ መ/ቤቶች የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውንና 2014 ዓ.ም. ግብር የከፈሉ 2015 ያደሰ።
- ተጫራቾች የእቃ አቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናችውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅርብ የሚችል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ የሚያቀርቡ ሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስክበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ የተረጋገጠ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማሲያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጥቃቅና አነስተኛ ኢንተርፐራይዝ ከአደራጃቸው ድርጅት የዋስትና ደብዳቤ ማምጣት ይኖሩባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ስነዱን የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ከላይ በተገለጸው ጽ/ቤት አድራሻ ቢሮ ቁጥር አንድ(1) በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በመንግሥት መ/ቤት የስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጅምሮ እስከ 16/12/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ከፍት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው በ16/12/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡30 እስከ 8፡oo ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር አንድ (1) ገቢ ማድረግ አለባቸው ጨረታው በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡oo ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል። ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት (ተጫራቾች) ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ሚኤሶ ወረዳ ገ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚገኝ መጋዘን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ብዛትና ጥራት አሟልቶ ግዴታ ማቅረብ አለባቸው።
- ለሽያጭ የቀረበውን ዕቃ ጥራቱ ያልጠበቀ ከሆነ አሸናፊው ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃውን የመለወጥ /ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት።
- የማስጫኛና የማስወረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የተሞላው ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ፈርማ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መኖር አለበት።
- ጽ/ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካኘ ጨረታውን በከፈልም ሆኖ ሙሉ በሙሉ መሰርዝ መብቱ ተጠበቀ ነው።
- ተወዳዳሪዎች ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጅምሮ ውሉን ከተፈራረሙ በኋላ ዋጋው የፀና ይሆናል።
አድራሻ፡- በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት
ሚኤሶ
ስልክ ቁጥር 0910 04 4850/0973 61 16 68
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ የገ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት
