የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ለ2015 በጀት ዓመት የመኪና ጎማዎች፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የህትመት አገልግሎት፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና የእጅ ዋጋ ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ለ2015 በጀት ዓመት በዞኑ በሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡-
1. የመኪና ጎማዎች
2. የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የኮንትራት
3. የህትመት አገልግሎት
4. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና የእጅ ዋጋ ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ፡-
• በዘርፉ የሚመለከተው የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤
• የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርትፊኬት ያላችሁ፤
• የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላችሁ፤
• የመኪና ጎማዎች ግዥ ሚፈፀመዉ ለአንድ ጊዜ ሲሆን ሌሎች እቃዎች ዓመታዊ የኮንትራት ግዥ እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ሆኖ ፈጣን አገልግሎት ለማግኘት ድርጅታችሁ ጎንደር ከተማ ቅርንጫፍ ሊኖረዉ ይገባል፤
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 22 በመምጣት የተሟላ የጨረታውን ዝርዝር
ማስታወቂያና ሙሉ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ። ጨረታው ጋዜጣው በወጣበት በ16ኛው ቀን በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተጠቀሰው ቦታ ቀንና ስዓት ይከፈታል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0581111309 (0581110420) ፋክስ ቁጥር 0581112041 መደወልና ፋክስ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ
