የቤት ሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ሙሴ መንበሩ እና በፍ/ባለ እዳ ወ/ሮ አበባ መንበሩ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የባለእዳው ንብረት የሆነውን በቡሬ ከተማ ቀበሌ 01 ክልል ውስጥ የሚገኘውን የፍርድ ባለእዳ ንብረት የሆነው በምስራቅ የእግር መንገድ ፣ በምዕራብ ሃረገወይን ካሳ ፣ በሰሜን እ/ይ ወርቅነሽ ፣ በደቡብ መንግስት የሚያዋስነውን ሁለት ክፍል ዶርም እና ሁለት ክፍል ዋና ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 791,825/ሰባት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃያ አምስት ብር/ ሆኖ በነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሆነው ቀጠሮ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል።
ስለዚህ የባለእዳውን ንብረት በጨረታ መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊው እንደታወቀ ከሽያጩ ገንዘብ ውስጥ ቢቻል ሙሉን ካልተቻለ ¼ ኛውን በፍ/ቤቱ በሞዴል 85 አደራ የሚያስይዝ መሆኑን እናሳውቃለን።
የምዕራብ ጐጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
