Tender Detail

Tender Details

  • Deadline15 Aug 2022, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printed Advertising Materials

አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ህትመት ማሳተም ይፈልጋል


የህትመት ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ የክልሉን ህዝብና የልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤና እና የስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሃገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበራችን በሁሉም የቀጠና ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች 86,000 /ሰማኒያ ስድስት ሺህ/ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ህትመት ማሳተም ይፈልጋል፡፡ ይህን ስራ ለመስራት በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶችን አጫርቶ ውለታ ኮንትራት በመስጠት በአጭር ጊዜ ውስጥ
ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
  2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። 
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከቢሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ./ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣
  6. ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር / አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር 100 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡30 ላይ ይታሸጋል በ9፡00 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
  7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  8.  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 100 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583207360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/

Save Tender