የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ ፣ የሞተር ብስክሌት ጥገና የእጅ ዋጋ ፣ ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ጥገናውንና የህትመት ስራውን ማሰራት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ በምዕ/ጐጃም አስተዳደር ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ 28ቱ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ በጀት አመታዊ ውል በመያዝ
- ሎት 1. የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ
- ሎት 2. የሞተር ብስክሌት ጥገና የእጅ ዋጋ
- ሎት 3. ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ጥገናውንና የህትመት ስራውን ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ጥቅል ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ በሜ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ/ንብ/አስ/ ቢሮ ቁጥር 38 መግዛት ይቻላል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር 1 በመቶ ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሜ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 38 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው የመዝጊያ ስዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስደም፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት /በድምር/ ዋጋ ይሆናል፡፡
- የሞተርና የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘመኑ የታደስ የብቃት ማረጋገጫ ማቅርብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ መሙያው ላይ ማህተምና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 38 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 0583300432 በተጨማሪ ስልክ ቁጥር0583300196 /0583300448 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
