Tender Detail

Tender Details

  • Deadline06 Aug 2022, 1:57 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Stationery Materials

በጉምሩክ ኮሚሽን ሞጆ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም ክር ፣ ካርቶንና ማዳበሪያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


በጉምሩክ ኮሚሽን ሞጆ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተተው ዕቃዎች ግልፅ የጨረታ ቁጥር ግ04/2015 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎችን በጉምሩከ አዋጅ 859/2006 ን ንዑስ አንቀፅ 1 እና በተሻሻለው ዮጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ | መሰረት ዕቃቸውን የጉምሩከ 5. ሥነሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ቃዎቻቸው እንደተተዉ ተቆጥረዋል፡፡ ስለሆነም በገቢዎች ሚኒስቴር 6. ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ያሉ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት ባወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም ክር ፣ ካርቶን እና ማዳበሪያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1.  ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት እና ዓርብ ከጠዋት 2፡oo ሰዓት እስከ ቀኑ 5:00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 5፡30 ሰዓት የማይመለስ ብር
    100 /አንድ መቶ| በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ 15% የተጨማሪ እሴት ታhስ (VAT) የምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.0 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የ15% የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባን በተረጋገጠ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው እንደታወቀ (3 (ሶስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ካሸነፉበት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COM– MISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን የግል ባንክ ከሆነ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ቅርጫፎች፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሆነ ደግሞ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርጫፎች መዘጋጀት አለበት፡ : ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅተው ማህተም ያረፈበት ሰነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. የግልጽ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ፤ የሞሉበት ሠነድ፣ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት ጠዋት 4:45 ሰዓት ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡
  5. የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  6. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:45 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፡፡
  8. ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጨረታውን ለማሸነፍ ሲል መደለያ የሰጠ ወይም ለስጠት የሞከረ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ይወገዳል፡፡ ጨረታው ከተካሄደ በኋላም ቢሆን ጨረታ አሸናፊው ጨረታውን ያሸነፈው በህገ-ወጥ መንገድ መሆኑ ከተረጋገጠ የጨረታው ውጤት ይሰረዛል፡፡
  9. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ ኣይችሉም፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  12. የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው፡፡ 05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባን በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡ ያሸነፉት ዕቃም በድጋሚ ለጨረታ ሽያጭ ይቀርባል፡፡
  13. በተራ ቁጥር 12 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
  14. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡
  15. . ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ ያቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡
  16. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-90-94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫ ጽ/ቤት

Save Tender