በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት አላቂ የጽዳት እቃዎች ፣ የጽህፈት መሳሪያ እና ሌሎች አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ ለሰራተኛ የሚሆን የደንብ ልብስና የተለያዩ የስራ ጫማዎች ሌሎችን እቃዎች ግዥና የተለያዩ አገልግሎት ይፈልጋል
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር /14/10/2014
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት በአስተዳደር ስር ለሚገኙ ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች
- አላቂ የጽዳት እቃዎች፣
- የጽህፈት መሳሪያ እና ሌሎች አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ለሰራተኛ የሚሆን የደንብ ልብስና የተለያዩ የስራ ጫማዎች፣
- ለቢሮ የሚሆን ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ለተለያዩ ስልጠና የሚውል መስተንግዶ፣
- ለተለያዩ ህትመት ስራዎች፣
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስና የፈርኒቸር እቃዎች ጥገና ፣
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት ሰርተፊኬት የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ህጋዊ ማስረጃ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።
- ተጫራቾ ከላይ ከተረዘሩት ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ዕቃዎችና ቁሳቁሶች የሚወዳደሩ ከሆነ ለእያንዳንዱ ዘርፍ ያወጡት ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡትን ሰርተፊኬት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት ሊስት ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች ከሆኑበት ጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁበትን እና ህጋዊ ሰርተፊኬት ከአደራጁ መስሪያ ቤት የተሰጣቸውን ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ ከሌሎች ዶክመንቶች ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በመደበኛ የስራ ሰዓት ከጽ/ቤቱ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመስሪያ ቤቱ ፍላጎት መሰረት ብቻ በመሙላት የተሟላ የመወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በሁለት የተለያየ ፖስታ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለበት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታ መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይንም ከጨረታ ራሱን ማግለል አይችልም።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆባቸውን እቃዎች እስከ መስሪያ ቤቱ የንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው መጓጓዣና የጉልበት ማቅረብ ይኖባዋቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 4183 በመደወል ወይንም ኦሎምፒያ አካባቢ ከጌቱ ማርሻል ሴንተር በጀርባ በኩል ከሚገኘው ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ህንፃ 2ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 መምጣት መጠየቅ ይቻላል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የፋይናንስ ጽ/ቤት
