ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በሪጅኑ በተለያየ አካባቢ የውጪ ማስታወቂያ ሥራ (Billboard) በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በሪጅኑ በተለያየ አካባቢ የውጪ ማስታወቂያ ሥራ (Billboard) በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ መለያ ቁጥር RFQ: - SER/ RSS/116/2022
በዚሁ መሰረት በህትመት እና ማስታወቂያ ዘርፍ ላይ የተሰማራችሁ፣ ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሁለት አመት የስራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 04 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ክፍል በመቅረብ ከተማ አዋሽ ባንክ ህንጻ ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
መስፈርት
1. ጨረታው ከሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ነሐሴ 04 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለዚህ በፊት በህትመት እና ማስታወቂያ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 20,000.00/ሀያ ሺህ/ የጨረታ ማከበሪያ የባንክ ሲፒኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸዉንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 04 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘገጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022 111 0994/022 112 1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ኢትዮ ቴሌኮም
ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
