የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ እማሆይ እህተፃዲቅ አስራት እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አልታዬ ተሰማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 81007 ቀን 15/6/2014 ዓ.ም. እና 13/4/2014 ዓ.ም. በመ/ቁ 86374 በ20/11/2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤ.ቁ. 611 የካ/ቁ1/45/378261/00 በእነ አቶ አልታዬ ተሰማ ስም የተመዘገበ በፕሮፖርሽን ከግቢ ውስጥ ለቤቱ የሚደርሰው የቦታ ድርሻ ስፋት 142 ካ.ሜ. ጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለግለሠቡ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 277 ካ.ሜ. የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 472,000(አራት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቁ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም።
በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪም ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
