የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተለያዩ ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ስዲግ/ግጨ003/2015
ተቋማችን የተለያዩ ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ. |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
የተለያዩ ዓይነት ህትመቶች
|
100,000.00 |
ነሐሴ 04 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ነሐሴ 04 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ፣ የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ያልታገደ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 204 በመምጣት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- አድራሻ፦- ፒያሳ ደጎል አደባባይ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ስታፍና ዲቪዥን ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 204 ስልክ ቁጥር 011-156-01-48
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና < ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY > በሚል መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን ፣ ሰዓት፣ እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
