Tender Detail

Tender Details

  • Deadline26 Jul 2022, 10:19 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት እነ ከበርኩ ተ/ማርያም እና በፍ/ባለዕዳ ሲ/ር ለምለም ደሳለኝ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ በመ/ቁጥር/298684 በ12/7/2014 ዓ.ም. እና በኮ/መ/ቁ/302431 በ5/9/2014 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 272 የሆነ ቤት የይዞታው ስፋት 175 ካ.ሜ. በይዞታ መለያ ኮድ AA000030200926 አዋሳኞች በሰሜን በኩል AA000030200922 በደቡብ በኩል AA000030200925 በምስራቅ በኩል AA000030200941 ያሉት በምዕራብ በኩል መንገድ የሚያዋስን የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,065,500 (አንድ ሚሊዮን ስልሳ አምስት ሺ አምስት መቶ ብር) የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብአሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥገቢ ማድረግ አለበት።

በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender