የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወ/ወ/ትምህርት ጽ/ቤት የሰኞ ገበያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የG+2 ጅምር ህንጻ ግንባታ በአልማ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወ/ወ/ትምህርት ጽ/ቤት የሰኞ ገበያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የG+2 ጅምር ህንጻ ግንባታ በአልማ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ለጨረታው ማሟላት የሚገባዎት፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት።
- የዘመኑን ግብር የከፈለ የከፈለች ፍቃዱን ያደሰ/ሰች።
- ቲን ነምበር ያላቸው መሆኑን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በስማቸው የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው።
- የመልካም ስራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ከታወቀ የመንግስት ተቋም ማቅረብ የሚችልና ላቀረበው የመልካም ስራ አፈጻጸም ጊዜያዊ/ፋይናል ርክክብ የተደረገበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የገቢዎች ክሊራንስ ያለው/ያላት ስድስት ወር ያላለፈው።
- ደረጃቸው G.C/B.C 6 እና በላይ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያለው/ላት።
- ማንኛውም ተጫራቾች የተጀመረ እና የማስረከቢያ የጊዜ ገደቡ ያላለፈና በተደጋጋሚ ውለታ በማራዘም። ፕሮጀክት ያላጓተተ/ች አለመሆናቸውን ከሚኖሩበት ወረዳ/ከተማ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-8 የዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
- ስለግንባታው ዝርዝር መረጃ ከመጫረቻ ሰነዱ ማየት ይችላሉ።
- በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ያልተሞላበት ክፍት ቦታ ካለ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል። እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ቀን በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው የሚከፈትበትን ሰዓት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ዋና እና ኮፒውን በማያያዝ ሁሉም ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ኦረጂናል ማህተም በመጠቀም በጥንቃቄ በ2 ፖስታ በማሸግ በወረዳው ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም ከላይ ከተራ ቁጥር 1-8 የተዘረዘሩትን ኦርጂናል ሰነዶችን በእጅ በመያዝ ለማመሳከሪያነት በዕለቱ ይዘው መገኘት አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም በህዝብ በዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከሚሸጠው የጨረታ መመሪያ ማየት ይችላሉ። እንዲሁም 033 116 01 99 መደወል ይችላሉ።
በአብክመ የደቡብ ወሎ መስ/ዞን
የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት
