የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጅማ ዲስትሪክት የእንጨት መሰንጠቂያ እና መሥሪያዎች ከጄኔሬተር ጋር በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
አንደኛ ደረጃ የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጅማ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ስርዓት አከራይቶት የነበረውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከተውን የእንጨት መሰንጠቂያ እና መሥሪያዎች ከጄኔሬተር ጋር በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
የተከራዩ ስም |
ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ |
የንብረቱ ዝርዝር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
ፈለገ ሰላም የእንጨት እና ብረታብረት ሥራ ኢንተርፕራይዝ |
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጂማ ዲስትሪክት ግቢ ውስጥ
|
|
1,574,405,18 |
ነሐሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ከ8:00-10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ
|
ማሳሰቢያ
- ከላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20) በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ በሐራጁ መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ማልከቻቸው ላይ 1ኛ ለንብረቱ የሚያቀርቡትን ዋጋ 2ኛ ለንብረቱ የሚከፍሉትን የቅድሚያ ክፍያ መጠን 3ኛ ቀሪ ክፍያውን ከፍለው የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ፤ በግልፅ በመጻፍ ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 10:00(ሰዓት) በፊት በጂማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት በጂማ ዲስትሪhት ጽ/ቤት ዉስጥ ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው በመገኘት ሂደቱን መከታተል ይችላሉ።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ በሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል ።
- አሸናፊዉ ያስያዘው ገንዘብ ከግዢዉ ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል።
- አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን በሊዝ ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ በሐራጁ ወቅት ያቀረበውን የቅድመ ክፍያ መጠን በቅድሚያ መክፈል እና የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መሥፈርት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማሟላት የማሺነሪ ኪራይ ዉል ካልተፈራረመ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል የቅድመ ክፍያ መጠኑም የማሽኑን ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት ሊያንስ አይችልም።
- የሐራጁ አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ የንብረቱን የሽያጭ ዋጋ ላይ 15 % ተ.እ.ታ (VAT) ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለበት እንዲሁም ከቀረጥ ነፃ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ወይንም በመንግስት የሚጠየቁ ማንኛውንም ቀረጥ መክፈልና ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
- ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጅማ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 047-111-0908 ወይም 047-111-0016 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልጉ ካሉ ከጅማ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መመልከት ይቻላል ።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጅማ ዲስትሪክት
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
