የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጅማ ዲስትሪክት የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች በድርድር ለመሸጥ ይፈልጋል
የድርድር ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጅማ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ስርዓት ለአቶ አሰጋኸን ተፈራ ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት አከራይቶት የነበረውን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ከባንኩ ጋር በገቡት የሊዝ ውል መሰረት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ባንኩ ማሽነሪዎቹን የተረከበ ሲሆን አሁን ላይ በድርድር ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
የተከራዩ ስም |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የሚሸጠው ንብረት ኣይነት |
የድርድር ሽያጭ መነሻ ዋጋ (ብር) |
የድርድር ሽያጭ ሳጥኑ የሚከፈትበት |
የድርድሩ ደረጃ |
|
አሰጋኸኝ ተፈራ ወሰን |
ጅማ ከተማ ውስጥ
|
|
1,988,329.91
|
ነሐሴ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ከ4:00 እስከ 6:00
|
4ተኛ
|
ማሳሰቢያ
- ከላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20) በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንh በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ በሐራጁ መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ማልከቻቸው ላይ 1ኛ ለንብረቱ የሚያቀርቡትን ዋጋ፤ 2ኛ ለንብረቱ የሚከፍሉትን የቅድሚያ ከፍያ መጠን 3ኛ ቀሪ ክፍያውን ከፍለው የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ፤ 4ኛ ለቀሪ እዳው የሚያቀርቡትን ዋስትና በግልፅ በመጻፍ ነሐሴ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 (ሰዓት) በፊት በጂማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጂማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ውስጥ ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው በመገኘት ሂደቱን መከታተል ይችላሉ።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ በሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
- አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል።
- አሸናፈው ተጫራች ንብረቱን በሊዝ ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ በሐረጁ ወቅት ያቀረበውን የቅድመ ክፍያ መጠን በቅድሚያ መከፈል እና የባንኩን የማሺነሪ ኪራይ መሥፈርት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማሟላት የማሽነሪ ኪራይ ውል ካልተፈራረ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል የቅድመ ከፍያ መጠኑም የማሽኑን ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት ሊያንስ አይችልም።
- የድርድር ሽያጩ አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ የንብረቱን የሸያጭ ዋጋ ላይ 15 % ተ.እ.ታ (VAT) ጨምሮ የመከፈል ግዴታ አለበት አንዲሁም ከቀረጥ ነፃ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ወይንም በመንግስት የሚጠየቁ ማንኛውንም ቀረጥ መክፈልና ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
- ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ጅማ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 047-111-0908 ወይም 047-111-0016 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልጉ ካሉ ከጅማ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መመልከት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ የድርድር ሽያጩን በከፈል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጅማ ዲስትሪክት
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
