የቤት ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሣሽ
1ኛ ብሩክታይ ሐሰን ጠበቃ ካሊድ ከበደ
2ኛ ከድር ሙስጦፋ እና በአፈ/ተከሣሽ አፈወርቅ አሰፋ መካከል ስላለው የገንዘብ/አፈፃፀም/ ክስ ክርክር ጉዳይ በቆቦ ከተማ ቀበሌ 03 ውስጥ በምስራቅ የጌታቸው አያሌው፣ በምዕራብ መንገድ፣ በደቡብ መንገድ፣ በእውቀት መለሰ የሚያዋስነው ቦታ ካርታ ቁጥር 2.2/1479/2009 ተመዝግቦ የሚገኘው የአፈፃፀም ተከሣሽ የአፈወርቅ አሰፋ ቤት ግምቱ ብር 525,104.19/አምስት መቶ ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ አራት ብር ከ19 ሳንቲም/ በሃራጅ ጨረታ ይሸጣል።
ስለዚህ የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያው ከሐምሌ 04 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ድረስ ይካሄዳል።
ስለሆነም በሐራጅ የጨረታው መሣተፍ/መግዛት/ የሚፈልጉ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈበትን 25 በመቶ ወይም ¼ ኛውን ለፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባለሙያ ወዲያውኑ ማስያዝ ያለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
