Tender Detail

Tender Details

  • Deadline31 Aug 2022, 4:20 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ ባለመብት ወ/ሮ ጤናዬ ፍቃዱ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አንተነህ አባተ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 155182 ፣ 100449 በ17/11/2011ዓ.ም. እና በግንቦት 12 ቀን 2011 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ ክ/ከተማ ቀበሌ 01 የቤ.ቁ. አዲስ የቤቱ ስፋት 160 ካ.ሜ. ይዞታ ውስጥ ከሚገኙ ቤቶች ውስጥ የፍርድ ውሳኔ ያረፈበትን ወደ ግቢ ሲገባ በስተቀኝ ያሉትን አራት ክፍል ቤቶች አጠቃላይ ይዞታ ስፋት 160 ካ.ሜ. ሲሆን የፍርድ ውሳኔ ላረፈበት አራት ክፍል ቤቶች በንፅፅር የሚደርሰው 76.56 ካ.ሜ. አራት ክፍል ቤቶችና የንፅፅር የሚደርሳቸው ይዞታው ሰነድ አልባ ንፅፅር ይዞታ የጋራ ግቢ የጋራ መግቢያ መውጫ ቦታ ያለው መሆኑ ታውቆ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 23,046.41 (ሃያ ሦስት ሺ አርባ ስድስት ብር ከአርባ አንድ ሳንቲም) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሀሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች
የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን  እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም
ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ ፣ ሐራጁ ጎድቶኛል
የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ፍ/ቤት

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender