Tender Detail

Tender Details

  • Deadline17 Jul 2022, 1:16 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicles Rent

አማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀላል ተሽከርካሪዎችን (Station wagon) በ2014 በጀት ዓመት በዘርፉ ተሰማርተው እየሰሩ ካሉ ህጋዊ አቅራቢ ድርጅቶች መካከል በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል



ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የጨረታ ቁጥር AWWCE 02/2014 ቀላል ተሽከርካሪዎችን (Station wagon) ብዛት 12 (አስራ ሁለት) በ2014 በጀት ዓመት በዘርፉ ተሰማርተው እየሰሩ ካሉ ህጋዊ አቅራቢ ድርጅቶች መካከል በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የተ.እ.ታክስ ምዝገባ ቁጥር እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት።
  2. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በመጫረቻ ቴክኒካል ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
  3. በአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ስም የተሰራ በሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል /Unconditional Bid bond/ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ ለተገለፁት ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡት ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የማቅረቢያ ጊዜያቸውን ውል በተያዘ ቢበዛ 120 ቀናት ውስጥ ማቅረብ የሚችል መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ኮፒ እና ኦርጅናል በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 32 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  8. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀናት ውስጥ ውል መፈረም ይኖርበታል።
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ህጋዊ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን በነፃ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 በሚገኘው የድርጅቱ ህንፃ 3ኛ ፎቅ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በደብዳቤ ለተጫራቾች ያሳውቃል ግን ተጫራቾች ደብዳቤያቸውን እንዲወስዱ በስልክ አድራሻቸው ተነግረው ካልወሰዱ እንደወሰዱ ይቆጠራል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 52 03 መደወል ይችላሉ።

አድራሻ ባህዳር ቀበሌ 14 ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ት/ቤት ጎን ወይም አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት

 

አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

Company Info
Save Tender