Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 Jul 2022, 12:13 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Services

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች ፍተሻና ሙሌት በሁለት ዓመት ውል ላይ የተመሠረተ የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


 የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/Re‐28/2014

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች ፍተሻና ሙሌት በሁለት ዓመት ውል ላይ የተመሠረተ የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ሰነድ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 115.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡: ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 0114420216

 

ፋክስ 0114420688

 

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ

Company Info
Save Tender