Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Jul 2022, 12:08 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Public Address Systems

የሆሣዕና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ለዕቃ ግዥ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ ማስተካከያ አድርጎበታል።


ተሻሽሎ እና ታርሞ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የሆሣዕና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ2014 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ዕቃ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ለዕቃ ግዥ የወጣ ጨረታ በዚህ የተስተካከለ መሆኑን እየገለጽን፤

ጨረታ ምድብ 03

  • ሎት 1. ኮሌጃችን የሳይንስ ትምህርቶች ቤተ-ሙከራን በተለያዩ ወል ቤንቾችንና ማውንትድ ካቤኔት ዕቃዎችን መግዛትና በቤተ-ሙከራ ሕንፃዎች ላይ የተከላ ሥራ ማድረግ፤
  • ሎት 2. የተማሪዎች ዶርም ተደራራቢ የመኝታ አልጋ ከነችፑድ የመቀመጫ ወንበር፣ የተለያዩ ጠረጴዛዎችን፤ እና ቁምሳጥኖች ግዥ
  1. በዘርፉ ወይም በንግድ ሥራ መስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው::
  3. የግዥው መጠን ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ሰ
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚለከታቸውን ማስረጃዎች የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  5.  የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፍኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ከላይ ለተጠቀሰው ጨረታ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን በሥራ ሰዓት ከሆሣዕና መም/ትም/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ከሎት አንድ እስከ ሎት ሁለት ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ፤ ኦርጅናል እና ኮፒ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ ሆሣዕና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆሣ/መም/ትም/ኮሌጅ አዳራሽ ይከፈታል፤ የሚከፈተው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  10. ኮሌጁ ስለ ግዥ አፈጻጸሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያም ይወረሳል፡፡
  12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 555 2650 ወይም 046 555 2651 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሆሣዕና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

Save Tender