Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Jul 2022, 9:54 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

ኢስት አፍሪካ አግሪ ቢዝነስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በርካታ ብረታ ብረቶች እና ያገለገሉ ጎማዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ማስወገድ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ኢስት አፍሪካ አግሪ ቢዝነስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በሚያስተዳድረው የጨዋቃ እርሻ ልማት ድርጅት ቅጥር ግቢ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት፤

  • በርካታ ብረታ ብረቶች ( ቁርጥራጭ ብረቶች፤ የተለያዩ አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ማሽኖች፤ ውድቅዳቂ ብረቶች….ወዘተ)
  • ያገለገሉ ጎማዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ማስወገድ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው  መሳተፍ ይኖርባቸዋል፤፤

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይኖርበታል።
  2. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ስፍራው ድረስ በመሄድ ዕቃዎቹን ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለብረታ ብረቶች ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ)፤ ለጎማዎች ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ) በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ብረታ ብረቱን የአንድ ኪሎ ግራም የሚገዙበትን ዋጋ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ተመዝኖ በተገኘው ጠቅላላ ብረታ ብረቱን ማንሳት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ጎማውን በጥቅል የሚገዙበትን ዋጋ ማቅረብ አለባቸው።
  7. በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች ሐምሌ 13  ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የጨረታ ዋጋቸውን ከሌሎች አስፈላጊ ፍቃዶች ፤ እና ለሚሳተፉበት ዕቃ የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ ጋር አብረው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ያስገባሉ።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተ.ቁ 7 በተጠቀሰው ቀን 5፤00 ዱከም /ደብረዘይት በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ይከፈታል።
  9. የጨረታ ማስከበሪያው ላሸነፉ ከሂሳቡ የሚታሰብ ሲሆን ለተሸነፉት ወዲያው ይመለስላቸዋል።
  10. ድርጅቱ ዕቃዎቹን ለማስወገድ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፤091 300 2915  ወይም  094 011 5733 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።

 

የጨዋቃ እርሻ ልማት ድርጅት ፤ ከአዲስ አበባ –መቱ–ጎሬ መስመር 650 ኪ.ሜትር ላይ ይገኛል።

 

 ኢስት አፍሪካ አግሪ ቢዝነስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ

Save Tender