የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለጅ+7 ህንጻ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለጅ+7 ህንጻ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች
- ሎት 2 የተለያዩ መጠን ያላቸው መስታወት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አሰራ አምስት/ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ የጨረታ መከፈቻ ቀኑ በበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመከፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያሰቀረውም፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የገበሩ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ በነፃ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሽያል ሰነዶችን ኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በመሙላት በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት የሞላው ጠቅላላ ዋጋ ከ 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፊኬት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ የጠ/ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የጠ/ዋጋ 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበውን መስታወት በራሱ ትራንስፖርት ጅ+7 ህንጻ ድረስ አቅርቦ መግጠም አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበውን የኤሌክትሪክ እቃ በራሱ ትራንስፖርት ኢንተርፕራዙ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበው እቃ በባለሙያ /ቴስት/ ተረጋግጦ ማለፍ አለበት፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ነው፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ባሉት 7 /ሰባት/የስራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለባቸው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ 0930958351 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደ/ማ ከተማ/አስ የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት
