የመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት መጠን ያላቸውን ኤች ዲ ፒ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ጎጃም ዞን በመርጡለ ማርያም ከተማ አስተዳደር የመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከፍተኛ የውሃ መስመር ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸውን ኤች ዲ ፒ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጥቅል ዋጋ ብር ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ብር 74,965.00 /ሰባ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አምስት ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባዋል፡፡
- የመነሻ ዋጋ HDPE PIPE OD 250 PN 10 1268.00 ብር /አንድ ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ ስምንት ብር/
- HDPE PIPE OD 250 PN 16 1890.00 /አንድ ሺህ ስምት መቶ ዘጠና ብር/ የመነሻ ዋጋ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያውን በጥሬ ገንዘብ ያስያዘ ተጫራች ክፍያውን ለጽ/ቤቱ በማቅረብ በጥሬ ገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የማይመለስ ብር 300/ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 16ተኛዉ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 4፡00 ድረስ በመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በመቅረብ ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተጫራቾች መመሪያ ጋር የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ በማካተት በእያንዳዱ ገጽ ፊርማና ማህተም በማድረግ ኦሪጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ ፣ ማህተም ማድረግና የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻ በማሸግና ሶስቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግና ከላይ የተጠቀሰውን አድራሻ በሙሉ በማጠቃለል ፖስታው ላይ በመጥቀስ በመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ተኛዉ ቀን እስከ 4፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዬ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ላይ ያላቸውን አስተያየት የጨረታ ቀኑ ከማለቁ 1 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ አቤቱታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ካለ ከጨረታ ውጭ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለተጨማሪ መረጃ ቢፈልጉ በመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0586660095 /0586660410/ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት
