Tender Detail

Tender Details


የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቧንቧ፣ የውሃ ቆጣሪ፣ ኬሚካል፣ ኤሌክትሪክ፣ ፓምፕና ሞተርና የደንብ ልብስ ግዥ

የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ለድርጅቱ ስራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ ማለትም ሎት1 ፒ.ንፒ. እና የፒ.ንፒ. መገጣጠሚያ እቃዎች፣ ሎት 2 የውሃ ቆጣሪዎች፣ ሎት 3 የኬሚካል እቃዎች፣ ሎት 4 ኬሚካሎች፣ ሎት 5 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት 6 የመካኒካል እቃዎች፣ ሎት 7 ፓምፕ እና ሞተር፣ ሎት 8 የደንብ ልብስ፣ ሎት 9 የደንብ ልብስ (ጫማ) እና ሎት 10 የስራ መሪዎች የደንብ ልብስ እቃዎችን በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችል
  4. የግዥው መጠን ከ200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
  6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ሮቢት በሚገኘው ዋናው ቢሮ (ቢሮ ቁጥር 06) ማግኘት ይችላሉ::
  7. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
  8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላት፣ የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ አይነት ለየይቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ 1 ኦሪጅናል እና 1 ኮፒ በመጠቀም 2 ሰነዶችን (ኦሪጅናል እና ኮፒ) በማድረግ ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ሮቢት በሚገኘው ዋናው ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ22ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ እንድያስገቡ እየገለጽን ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን ነገር ግን 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ሲሆን (ሎት 7 ፓምፕ እና ሞተር) ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ ሆኖ በ31ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ እንድያስገቡ እየገለጽን ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ነገር ግን 31ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን::
  9. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ሲገለጽለት የውል ማስከበሪያ 10% ብር በሲ.ፒ.ኦ/በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል::
  10. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
  12. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 092020146፣ 0914613590፣ 0989887862 ደውለው ማግኘት ይችላሉ::
  13. የጨረታው ውድድር በእያንዳንዱ ሎት ጥቅል ድምር ነው::

የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Summary
Dessie City Water Supply and Sewerage Service Enterprise invites bids in ten lots: pipes and fittings, water meters, chemicals, electrical and mechanical items, pumps and motors, and staff uniforms and shoes.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender