የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የመኪና ጎማ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ፈርኒቸር ለመግዛት ያወጣው ግልጽ ጨረታ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የክልል ም/ቤት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤንሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ፣ የመኪና ጎማና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- በጨረታው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት / የታደሰ ንግድ ፈቃድ የተመዝጋቢነት /የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከዋናው ጋር የተመሳከረ ፎቶ ኮፒ ከሰነዶቹ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከዋናው ጋር የተመሳከረ ፎቶ ኮፒ ቴክኒካሉንና ፋይናንሻሉን በተለያዩ ሁለት ሁለት በሰም በታሸጉ ፖስታዎች ከሰነዳቸው ጋር አያይዞ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የጨረታ መነሻ ዋጋውን 3% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከተገለፀው የጨረታ መነሻ ዋጋ ከ3% በታች የሚያቀርቡ ተጫራቾች በመጀመሪያ የቴክኒክ ግምገማ ውድቅ ይደረጋሉ፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች / ድርጅቶች ከታወቁና ውል ከተፈረመ በኋላ ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት /CPO/ መልሰው መውሰድ ሲችሉ አሸናፊ ድርጅቶች ለውል ማስከበሪያ የሚውል አሸናፊ የሆኑባቸው ዋጋ 10% በማስያዝ መጀመሪያ ያስያዙትን /CPO/ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ሙሉ ሰነድ ከየካቲት 12 ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘው ፕላን ኮሚሽን እና ግዥ ንብረት አስተዳደር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ የሰነድ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ ማስታወቂያው በወጣ በ15ኛው ቀን መጨረሻ ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913909956 /0911020435
የቤንሻንጉል ጉሙዝ መንግስት
የክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት
Summary
The Benishangul-Gumuz Regional Council Office buys vehicle tires, electronic equipment and furniture for the 2019 E.C. budget year. Bidders need a renewed licence, supplier registration, TIN and VAT registration.
