Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Address , Phone: 0926384778/0916497990
  • Website
  • Deadline12 Dec 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 300 ለእያንዳንዱ ሎት (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1፡ ብር 20,000 (CPO)
  • opening dateበዚያው ዕለት ከጠዋቱ 8:30 ሰዓት
  • Sector Vehicle and Spare Parts , Three-Wheeler, Motorcycle and Bicycle Purchase

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት በሚከተሉት ሎቶች የተደራጁ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

1. የጨረታው የዕቃ ዝርዝር

  • ሎት 1፡ ሞተር ሳይክሎች የቤንዝንና የኤሌክትሪክ

2. የተጫራቾች ብቃትና መስፈርቶች

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል:-

  1. በየዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
  2. የቫት (VAT) ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ አለባቸው።
  4. የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ከላይ ከተጠቀሱት በቁጥር 1-4 ያሉትን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

3. የጨረታ ሰነድ ግዢት

ጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 07 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

4. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security)

ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ (CPO) በሚከተለው መሠረት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስም አዘጋጅተው ማቅረብ አለባቸው።

  • ሎት 1፡ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር

5. የጨረታ ሰነድ አቀራረብ

ተጫራቾች የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን በተለያዩ በሰም በታሸጉ ኤንቨሎፖች ውስጥ በማስቀመጥ፣ ኦሪጅናል አንድ (1) እና ኮፒ ሁለት (2) በማዘጋጀት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

6. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ጊዜ

የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ከተቆጠረ በኋላ፣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 6:00 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ይዘጋል። ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የመዝጊያውና የመክፈቻው ቀን የሕዝብ በዓል ወይም የሥራ ዕረፍት ቀን ከሆነ፣ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተገለጹት ሰዓታት ይከናወናል።

7. የዕቃ ናሙና ማቅረብ

መ/ቤቱ ናሙና ማቅረብ የሚጠይቅባቸውን ዕቃዎች በጨረታው ሰነዱ ውስጥ ይገልጻል። ተጫራቾችም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለተጠየቁት ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

8. የዕቃ ማጓጓዣ

የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎችን በራሱ ወጪ በማጓጓዝ መ/ቤቱ ወደሚያመለክተው መጋዘን ማስገባት አለበት።

9. የጨረታ ውጤት

የጨረታው ውጤትና አሸናፊነት በጨረታ መመሪያው መሠረት ለተጫራቾች በማስታወቂያ ይገለጻል።

10. የመ/ቤቱ መብት

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥሮች:- 0926384778/0916497990

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

Summary
Central Sidama Zone High Court (Sidama Region) invites open bids to supply petrol and electric motorcycles for office use.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender